የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ የምርምር ንድፈ ሀሳቦች/ፕሮፖዛሎች/ ላይ የምርምር ንድፈ ሀሳቦችን ማቅረብና የአቻ ግምገማ በማካሄድ ላይ ነው

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ለ2015 ዓ.ም ፈንድ ሊደረጉ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ለማሳለፍ በኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች በተገኙበት የምርምር ንድፈ ሀሳቦችን ማቅረብና የአቻ ግምገማ ከነሀሴ 03/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በጠዳ ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሾች በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ስድስት የትምህርት ክፍሎች በየዘርፉ በሶስት በመከፋፈል የምርምር ፕሮፖዛሎች፣ የቴክኖሎጅ ሽግግርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ከቀረቡ በኋላ የአቻ ግምገማ እንደሚካሄድ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ህትመት አስተባባሪ ዶ/ር አሰፋ ጥላሁን ገልፀዋል።

Start Time

12:00 am

August 19, 2022

Finish Time

12:00 am

October 20, 2023